የመጨረሻው መጀመሪያ?

የመጨረሻው መጀመሪያ?

Author: Tatek Mamecha October 2, 2019 Duration: 26:03

የዛሬ 27 አመት ገደማ የዩጎዝላቪያ ተወዳጅ ሙዚቀኞችና የስነ ጥበብ ባለሙያዎች በሚያዘጋጁት የሰላም ኮንሰርት የሚታደሙ ሁሉ በአንድ ነገር እርግጠኞች ነበሩ። በዩጎዝላቪያ ጦርነት ሊከሰት አይችልም፥ ሊኖርም አይገባም የሚል ከፍተኛ እምነት ነበራቸው።

ይሁንና፥ በጥቂት ፅንፈኛ ፓለቲከኞች የተመራው የጥላቻና የማስፈራራት ዘመቻው አሸናፊ ወደሌለው የለየለት ጦርነት ሃገሪቷን ማግዶ በሁለተኛው የአለም ጦርነት ናዚ/ፋሽስት በአውሮፓ ካስከተለው እልቂት ወዲህ በአህጉሯ ታይቶ የማያውቅ እልቂት፥የሰዎች ጭካኔ፥የዘር ማጥፋትና ማፅዳት በሰፊው ተካሔደ፥ ዩጎዝላቪያም እንደ ሃገር መቆም ተሳናት በሗላም ፈረሰች።

በዚህ ባጠቃላይ ወደ 11 ዓመት በፈጀ ተከታታይና የተወሳሰበ ግጭት ወደ 2መቶ ሺህ በአብዛኛው ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲሞቱ ተፈረደባቸው። ከ4 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ነዋሪዎቿም እስከዛሬ ላልተቋጨ ስደት ተዳረጉ። ሌላም ሌላም ብዙ መከራ ደረሰ።


ጤና ይስጥልኝ። The Ethio Balkan Show የሚለው ይህ ፓድካስት በታጠቅ ወንድሙ ማመጫ ተቀምጦ ለእርስዎ የሚዘጋጅ ሲሆን፣ በኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ውስጥ ሊነሱ እና ሊወያዩ የሚገቡ የተለያዩ ጉዳዮችን ያቀርባል። እያንዳንዱ ክፍል ጥናትና ምርምር የተደረገባቸውን ርእሰ ጉዳዮች በመያዝ ለመስማት፣ ለመሳተፍ እንዲሁም ለመነጋገር አጋጣሚ ይፈጥራል። ይህ ፕሮግራም በማህበረሰብና ባህል ዙሪያ ያሉ እውነተኛ ውይይቶችን ለማሰራጨት የተመሠረተ ነው። የዚህ ፓድካስት ዓላማ የጋራ ሀሳብን በመጋራት እና በመረዳዳት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ አድማጮች እንደ አካል ተሳትፈው ሊነጋግሩ ይችላሉ። ታጠቅ ወንድሙ ማመጫ እንደ አዘጋጅና አቀራረብ ሰው የሚያቀርበው ይህ ዝግጅት ቀላልና ተወዳጅ በሆነ መልኩ የተዘጋጀ ነው። ፕሮግራማችንን በማውረድዎና በማዳመጥዎ ያሳየችሁን ድጋፍ በጣም እናመሰግናለን። በየሳምንቱ አዲስ ክፍል በመቅረብ ላይ ስለሆነ፣ ለማንኛውም አይነት ውይይት ክፍት መሆኑን እናስታውስዎታለን። ይህን ፓድካስት በማዳመጥዎ የሚያገኙት ሀሳብ እና እውቀት በዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ውስጥ ጠቃሚ እንዲሆን ተስፋ እናደርጋለን። የኢትዮጵያን ማህበረሰብ እና ባህል በሚመለከት የሚነሱ ጥያቄዎች እና ርእሰ ጉዳዮች በዚህ መድረክ ላይ በተፈጥሮነት ይወያያሉ። እንደገና እንገናኝ።
Author: Language: Oromo Episodes: 4

The Ethio Balkan Show
Podcast Episodes
ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm) [not-audio_url] [/not-audio_url]

Duration: 40:16
ከማዕበሉ በፊት ትናንሽ ማዕበሎች (Storms Before the Storm) ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮቼ! እንኳን ወደ ኢትዮባልካን ፖድካስት በሰላም መጣችሁ። በዛሬው ፕሮግራማችን የዩጎዝላቪያ ፅንፈኛ የብሄር ፖለቲከኞች ስትራተጂና አካሄድ፥ መሰረታዊ ፀባያትና አላማችንን ያሳካልናል ብለው ከተጠቀሟቸው ዘዴዎች መካከል ዋና ዋናዎቹን እንመለከታለን። ሃሃ፥ Mo…
ጽንፈኞች ጽንፈኞችን አዋለዱ: ተቋማትንም በጋራ አመከኑ የብሄር ፖለቲካውም ከሀይማኖት ልዩነቶች ጋር እንዲዛመድ ሆነ [not-audio_url] [/not-audio_url]

Duration: 28:57
እነሆ ኢትዮባልካን ክፍል 3 የሰርብ ጽንፈኞች የሌሎች ብሄር ጽንፈኞችን አዋለዱ; ተቋማትንም በጋራ አመከኑ የብሄር ፖለቲካውም ከሀይማኖት ልዩነቶች ጋር እንዲዛመድ ሆነ; ዩጎዝላቪያውያንም መግቢያ መውጫው ጠፋቸው:: ኢትዮባልካንን ያድምጡ: ይከታተሉ: ያካፍሉ
የታላቁ መሪ ማለፍና የፅንፍ ፖለቲካ ጂኒ ከሳጥኗ መውጣት [not-audio_url] [/not-audio_url]

Duration: 35:40
እነሆ Ethiobalkan Episode II. ጤና ይስጥልኝ ፥ ጤና ይስጥልኝ ፥ ጤና ይስጥልኝ ኣድማጮቼ! በክፍል አንድ ፕሮግራማችን በአንድ አገር ውስጥ የርስ በርስ ጦርነት እንዴት ማንም ሳይፈልገው ይቀሰቀሳል? በሚል ጥያቄ ጀምረን የዛሬ 27 አመት ገደማ የዩጎዝላቪያ አብዛኛው ህዝብ ሳይፈልገውና ሳያስበው አሸናፊ ወዳልተገኘለት የለየለት ጦርነት ሃገ…